በግብዣ ሐረር የመጡት ባለሙያ የክልሉን...
Last Updated on Tuesday, 03 November 2009 11:31 Written by Admin1 Tuesday, 03 November 2009 11:27
በአሰግድ ተፈራ
በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ግብዣ ከካናዳ የመጡት ባለሙያ በሐረር ክልል የደረሰባቸውን በደል ማዕከላዊ መንግሥት ሊመረምረው እንደሚገባ አመለከቱ፡፡
ከሃያ አራት ዓመት በላይ በዓለም የጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍና አሁን ደግሞ በሂድን ድራውት ድርጅት የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው እየሰሩ ያሉት ዶ/ር አብዱላዚዝ አዲሽ እንዳስታወቁት ከካናዳ ጠቅልለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት በቃል ጥበቃ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ በ29/8/99፣ በቁጥር 21599/20/80/99 በላኩላቸው የጥሪ ደብዳቤ ነበር፡፡
የሐረር ጤና ኮሌጅ ነርሶችን በየዓመቱ ቢያስመርቅም ከክልሉ ፍላጎት በላይ በመሆኑ ወደ ሌላ ክልል ስለሚሄዱ፣ ክልሉ ነርሶች አሰልጥኖ ወደ ሌሎች በመላኩ በየዓመቱ ለከፍተኛ ወጪ በመዳረጉ ኮሌጁን ትርፋማ ለማድረግ በተያዘ አቅድ በተለይ በኒውትሬሺን (ስነ ምግብ) ትምህርትን ባለሙያ ከሆኑት ከዶ/ር አብዱላዚዝ ጋር በሽርክና ለመስራት ከስምምነት መደረሱን በሁለቱ አካላት የተዘጋጀው የመግባቢያ ሰነድ ያስረዳል፡፡
በ29/8/99 ዓ.ም የክልሉ ጤና ቢሮ “አብረን እንስራ” በማለት ደብዳቤ ፃፈ፡፡ በ10/1/2000 ፕሬዚዳንቱ የወከሉዋቸው የጤና ቢሮና የፕሬዚዳንቱ የኢኮኖሚ አማካሪ ለስምምነቱ መነሻ የመግባቢያ ሰነድ አዘጋጅተው መግባባት ላይ መደረሱ ተገለፀ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ትምህርቱን በ2000 ለመጀመር ቅስቀሳ ተጀምሮ እንደነበር ዶክተር አብዱላዚዝ አስረድተዋል፡፡
ነሀሴ 24 ቀን 1999 ዓ.ም የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በጻፉት ደብዳቤ ““.የክልሉ መንግሥት ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የኢንቨስትመንት ፖሊሲን መሰረት ባደረገ መልኩ ተግባራዊ እንዲደረግ አስታውቃለሁ” በማለት ወደ ሥራ እንዲገባ ለጤና ቢሮ ደብዳቤ ይፅፋሉ፡፡ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ደብዳቤ ቢፅፍም ወደተግባር ከመግባት ይልቅ ጉዳዩ እንከን ገጠመው፡፡
እንደ ዶክተሩ ገለፃ አብረው ለመስረት በግብዣ ከመጡ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አልተቻለም፡፡ አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ አላገኙም፡፡ እንደ እሳቸው ገለፃ የጠሯቸው የክልሉ ፕሬዚዳንትም ሊያስተናግዷቸው አልቻሉም፡፡ የጤና ቢሮውም “አይመለከተኝም” በማለት ቁርጥ ያለ መልስ እንደሰጣቸው የገለጹት ዶክተሩ “ካናዳ ከነበረኝ የተስተካከለ ኑሮ ጓዜን ጠቅልዬ ከወጣሁ በኋላ የደረሰብኝ በደል መነሻው ምን እንደሆነና የትኛው አካል ላይ ችግር እንዳለ ሊገባኝ አልቻለም” ብለዋል፡፡
በሶማሌ፣ በአፋር፣ በትግራይና በአብዛኛው የአገሪቱ የገጠር ከተሞች ከፍተኛ ችግር የሆነውን የምግብ ንጥረ ነገሮች ጉድለት ችግር በመቅረፍ የኒውትሬሽን ባለሙያዎችን በማፍራት ከኮሌጁ ጋር ለመስራት መጥተው ያልተሳካላቸው ዶ/ር አብዱላዚዝ መሬት በሊዝ ገዝተው ለመስራት ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡
ቦታ እንዲሰጣቸው በጠየቁት መሰረት በሊዝ በወጣ ጨረታ ቀበሌ 18 አራተኛ ሞቢል ፊት ለፊት በጨረታ መሬት አሸንፈው በደረሰኝ ቁጥር 133397 447”40 ብር ቅድመ ክፍያ ለከተማ ቦታ አስተዳደር ካስገቡ በኋላ መሬቱን ሲያጥሩ ቦታው ለሦስተኛ ወገን መሰጠቱ እንደተገለፀላቸው ዶክተሩ አስረድተዋል፡፡ ይህንን ችግር “ሁለተኛ በደል” ብለውታል፡፡
“አብረን እንስራ ብለው ጠሩኝ፡፡ ሳይሆን ቀረ በጨረታ በሊዝ ቦታ ገዛሁ ለሦስተኛ ወገን ተሰጠ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ምክንያቱ አልተነገረኝም” የሚሉት ዶ/ር አብዱላዚዝ ጉዳዩን ይፋ ሳያደርጉ ከ1 ዓመት በላይ በትዕግሥት የቆዩት በሐረር ከተማ በሚኖሩት ቤተሰቦቻቸው ላይ ችግር ይፈጠራል ከሚል ስጋት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የመሬቱ ጉዳይ ሳይሆን ዋናው ችግር መንግሥትና አንዳንድ ክልሎች የሚሉትና በሐረር ያለው አሰራር አለመጣጣሙ እንደሆነ ያመለከቱት ዶክተሩ መንግሥት ኪሳራቸውን፣ የደረሰባቸውን በደል ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ አይይዘውም የፌዴራል መንግሥት ባለስልጣናትና ሌሎች ክልሎች ሊረዷቸው ቃል እንደገቡላቸው ገልፀዋል፡፡
የአፍሪካ ሂድን ሀንገር ፕሮግራም የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው እየሰሩ ያሉት ዶ/ር አብዱላዚዝ ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት “መረጃ አልሰጥም” ሲል የጤና ቢሮው ጉዳይ እንደማይመለከተው አስታውቋል፡፡ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ በበኩሉ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም፡፡