Wednesday Sep 08

Koromi


Amana Weldach




Amana kids was established to help eliminate some of the deprivations orphan children face in and around Harar. In 1995 we reached out to five kids. Today, we have reached 21 children ranging from kindergarten to seventh Grade. Their ages range between 3 and 15 with complete gender equality. Amana will add an additional 5 to10 kids annually until the future goal of 500 kids is reached.

Harar

 

የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ 39ኛ መደበኛ ስብሰባውን በሀረር ከተማ አካሄደ፡፡

Attention: open in a new window. PDFPrintE-mail


የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለ3 ቀናት ባካሄደው ስብሰባው የድርጅቱን የ2002 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጦ ከመረመረ በኋላ ከማፅደቁም በተጨማሪ በግንቦት 2002 አራተኛው አገራዊ ምርጫ የሊጉን ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገምግሟል፡፡


በዚሀም መሰረት ባለፈው አመት የድርጅቱን እቅድ አፈፃፀም አስመልክቶ በተለያዩ መስኮች አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ መቻሉን ያስገነዘበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በክልሉ በተካሄደው ምርጫም በሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ ድልን መቀዳጀቱን ገልጿል፡፡

ለቀጣይ የክልሉ መንግስት የሥራ ዘመን አሸናፊ መሆኑ የሊጉን ጠንካራ እንቅስቃሴ ከማመላከቱም ባሻገር ከፍተኛ ህዝባዊ አደራ የተጣለበት አጋጣሚ በመሆኑ በበለጠ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ ግንዛቤ ወስዷል፡፡


ከዚህም በተጨማሪ የሊጉን ቀጣይ የ5 ዓመታት መርሃ ግብር ስትራቴጄዎች እና የ2003 የሥራ ዘመን የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያም በሰፊው መክሯል፡፡ማሻሻያዎችንም በማከል አጽድቋል፡፡


የሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሊጉን 5ዓመታት የቀጣይ አመታት መርሃ ግብር አስመልክቶም የሐረር ህዳሴን መሰረት ያደረገና የሚሊኒየሙን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችለው ስልት መንደፉን ጠቁሟል፡፡ ሊጉ በቀጣይ አመታት የህዝቡን አደራ በተገቢው ለመወጣት በሚያስችለው ስልቱም መሰረተ ሰፊና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገትን ለማስፈን፤ የክልሉን እምቅ የልማት አቅም ለመጠቀም የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የልማት አጋዥ ሃይል እንዲሆን  ለማድረግ፣ በማህበራዊ ልማት መስክ ጥራትና ሽፋን ለማሳደግ እና የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን ለማጠናከር በነደፋቸው የስትራቴጂ ማዕቀፎች ዙሪያ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ  ይፋ አድርጓል፡፡


በተለይም የሊጉ የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ በመሬት አስተዳደር ጉዳይ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ያስተላለፈውን ውሳኔና የወሰደውን እርምጃ ሙሉበሙሉ ተቀብሎት እየተተገበረ ያለውን የመሬት አስተዳደር ያፈፃፀም ሄደቶችን በተመለከተም ችግር ፈቺ መዋቀራዊ አደረጃጀት በመዘርጋት የማጥራት ሄደቱን እንደሚቀጥል በአፅኖት አስገንዝቧል፡፡


በሌላ በኩልም ሊጉ የውስጠ ዲሞክራሲ ስርአት ግንባታውንም በጥልቀት የመረመረ ሲሆን በየጊዜው እያዳበረው ያለውን የአመራርና አሰራር ሂደቱን ይበልጥ ለማጎልበት የጥገኝነትና የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን ለማድረቅ የሚያስችለው የግምገማ ስርአት ዘርግቶ በመተግበር ላይ መሆኑን ከማስረዳቱም በተጨማሪ ለሂደቱም ቀጣይነትና ጥንካሬ  በቁርጠኝነት መነሳቱ ሊሰመርበት እንደሚገባ የሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴው አክሎ ገልጿል፡፡

Translate



My Favorite Video

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday240
mod_vvisit_counterYesterday528