ነባር ቅርሶች ጥንታዊነታቸውን ይዘው ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ ህብረተሰብ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተጠቆመ፡፡
Last Updated on Sunday, 18 July 2010 08:20 Written by Admin1 Sunday, 18 July 2010 08:18
Harari Mass Media
ነባር ቅርሶች ጥንታዊነታቸውን ይዘው ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ ህብረተሰብ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተጠቆመ፡፡
በሀረር አዳ ቤት ከህብረተሰብ ለተውጣጡ አካላት የግንዛቤ አውደ ጥናት ተሰጥቷል፡፡
ሀረር በአለም አቀፍ የሳይንስ የትምህርትና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እ.ኤ.አ በ2006 በአለም ቅርስነት ተመዝግባለች በዚያን ወቅትም ቅርሶቹ ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ አግኝተው ለትውልድ እንዲተላለፉና ለጥናትና ምርምር አገልግሎት የሚውሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተገባ ቃል አለ ይህንንም ለማስፈፀም የክልሉ መንግስት ከGTZ ጋር በመተባበር ከህብረተሰብ ለተውጣጡ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት የተሰጣቸው፡፡
የአለም አቀፍ ቅርስ አካል የሆነው የጀጎል ግንብ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ መንግስት ብቻውን የሚያደርገው እንቅስቃሴ በህብረተሰብ መደገፍ እንዳለበት የገለፁት የጀጎል ቅርስ ተንከባካቢ ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም አብዱረህማን ህብረተሰብ ቅርሱን ከተንከባከበ ሀረር የቱሪስት መዳረሻነቷ ይሰፋል ብለዋል፡፡
ነባር ቅርሶች ጥንታዊነታቸውን ይዘው እንዲቆዩ ህብረተሰቡ በመንከባከብና ቅርሶቹን ያለ አግባብ ለማደስ ባለመሞከር ቅርሶቹ ያላቸውን ይዘት ይዘው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡
ከGTZ ተወክለው የመጡት የከተማ ቀያሽና አርክቴክቸር ወ/ሮ ገብሬሏ ማርች የጀጎል ግንብን መልሶ መገንባት. ታሪካዊ ህንፃዎችን እንዴት ማደስና መልሶ ማቋቋም የሚቻልበትን መንገድና ታሪካዊነቱን ሳይለቅ ማቆየት የሚቻልበትን መንገድ ከህብረተሰብ ጋር ተወያይተውበታል፡፡














