በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ የሚካሄደውን የልማት እንቅስቃሴና መልካም አስተዳደር በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
Last Updated on Tuesday, 29 June 2010 19:01 Written by Admin1 Tuesday, 29 June 2010 18:43
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
በካናዳ እየተካሄደ ባለው የቡድን ሃያ አገሮች ስብሰባ ላይ ለመካፈል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካናዳ ቶሮንቶ የሚገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የልማት እንቅስቃሴና ሀገሪቱ የአፍሪካውያንን ጥቅም ለማስጠበቅ በአለም አቀፍ መድረኮች የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
በካናዳ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩና በቶሮንቶ ለድጋፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን እንዳሉት በኢትዮጵያ የሚታየው መልካም የልማት ስራ የሀገሪቱን ገፅታ በመለወጥ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ይህንኑ ጥረት ለመደገፍ የሚያስችላቸውን ተግባራት እያከናወኑ መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ እያሳዩት ያለውን የአመራር ብቃት እናደንቃለን ጠቅላይ ሚኒስትራችን የአፍሪካ ጀግና ናቸው እንዲሁም በ4ተኛው አገራዊ ምርጫ የውጪ ሃይሎችን ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ ኢትዮጵውያኑ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
አቶ ኪዳኔ አፈወርቅና ሌሎች የአፍሪካውያን ፍላጎትና ጥቅም በአለም አቀፍ መድረኮች ለማስጠበቅ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚያደንቁ ገልፀዋል፡፡















