በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2002 የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀረበ
Last Updated on Tuesday, 29 June 2010 18:43 Written by Admin1 Tuesday, 29 June 2010 18:36
በመልካም አስተዳደር እና መሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችለውን መሪ እቅድ በማዘጋጀት በከተማው ሁለንተናዊ እድገትና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጅምር ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የ2002 የዘጠኝ ወር ሪፖርት አቅርቧል፡፡በ2002 የዘጠኝ ወር ከተከናወኑ ስራዎች የጌጤኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ የጎርፍ መከላከያ ግብ ፕሮጀክት የቀላዳንባ ገበያ መአከል ግንባታ፣ ከሻሽ ጋራዥ- ቢራ መንድ ስራ፣ ከቀላዳንባ - ሙጢ መንገድ፣ የጀጎል ውስጥ ለውስጥ እና በጀጎል የሚገኙ የአስፓልት መንገገዶች በአጠቃላይ የመንገዶች ሥራ ከ75% እስከ 95% ተከናውነዋል፡፡
የፅዳት ስራ፣ የሙከራ ትግበራ በጀጎል ውስጥ በ50 ሰራተኞች ሲሰራ የነበረው በ26 ሰዎች ተከናወነ ሲሆን በሌላ በኩል ባለልኳንዳ ቤቶች በማህበር ተደራጅተው የቄራ አገልግሎት አሰጣጡን ደረጃ ለማሻሻል ብር 60,000.00 በሚገመት የክርስቲያን ቄራ እድሳት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡
የቀበሌ መዋቅራዊ ትስስርን ፈር ማስያዝ የዘጠኝ ወር ዋንኛ አላማ ሲሆን ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከዋናው የስራ ሂደት አስከ ቀበሌ ያለው አገልግሎት ወጥነት ባለው መልኩ እንዲደራጁ የሚያስችል የክለሳ ሥራ መጠናቀቁን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
የ2001 ዓ.ም የዘጠኝ ወር ገቢ ከ2002 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፃር የ2002 ገቢ 2,809,770.01 ብር ብልጫ ወይም በ32% የገቢ እድገት አሳይቷል፡፡
የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2002 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት የልማት ስራዎች እንቅስቃሴ (ሪፖርት)
















